እንኳን ደስ አላችሁ!

የላቀ ስኬትና የእውቅና መግለጫ

የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባሳየው የላቀ የሥራ አፈጻጸምና በተመዘገበው አንጸባራቂ ውጤት በአማራ ክልል 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የልዩ እውቅና ተሸላሚ ሆኗል።

ይህ ኩራት የሚሰጥ ታላቅ ስኬት እውን ሊሆን የቻለው በመምሪያውና በተዋረድ ባሉ አመራሮችና ሰራተኞች የጸና ትጋት እንዲሁም ከየደረጃው ከሚገኙ አጋር አካላት ጋር በተደረገ የተቀናጀ ጥረት በመሆኑ፡

ለመምሪያውና በተዋረድ ላሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች—ላሳያችሁት ከፍተኛ የሙያ ፍቅር፣ ተነሳሽነትና ውጤታማነት፤

ለዞናችን ህዝብና አጋር አካላት—ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ድጋፍና ቀጣይነት ያለው ትብብር፤የከበረ ምስጋናችንንና ወሰን የሌለው አክብሮታችንን እንገልጻለን።

ይህ በክልል ደረጃ የተመዘገበው የወርቅ ዋንጫ ድል፣ በቀጣይም የዞናችንን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ወደ ላቀ የዕድገት ማዕረግ ለማሸጋገር ትልቅ መነቃቃትንና አቅምን ይፈጥራል።

እንኳን ደስ አለን!
የደቡብ ወሎ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

Was this helpful?