ከደሴ 228 ኪ.ሜ ከወረዳዉ ሳይንት ከተማ አጅባር በስተሰሜን ምስራቅ 25 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በ11° 06′ 87″ ከምድር ወገብ ሰሜንና 30° 45′ 20″ ምስራቅ ጅ.ፒ. ኤስ ከባህር ጠለል ወለል በላይ 8,458 ጫማ ላይ ትገኛለች፡፡ መንገዷነዉ፡፡
ከደሴ 225 ኪ.ሜ በመኪናና 3 ኪ.ሜ በእግር ደብሯ ዙሪያዋ ገደል ሆና በግራና ቀኝ በጉንዳና ገዳማይ ጅረቶች እንዲሁም በሽሎ ወንዝ ታጅባ የምትገኝ ዉብ የታሪክ አምባ ነች፡፡ አምባዉ ለመዉጣት 12 በሮች አሉት፡፡ ፊትበር፣ ቦካ፣ ገተም፣ ሞገራ ግራኝ፣ ታሪኳ፣ የዘንጌ፣ አሳስት፣ አጎና፣ አምጣ ፈረሴን፣ አህያ መደብለያ እና የጌለት ናቸዉ፡፡ አምባዉ ላይ በዩሀንስ ራዕይ ላይ የ7ቱ ቤተ-ክርስቲያን አምሳያ 7 ቤተክርስቲያኖች አሉ፡፡
ይህች ገዳም በኢትዬጵያ መስዋዕት ኦሪት ከተሰዋባቸዉ አራት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አክሱም ጺዬን፣ ተድባበ ማሪያም፣ መርጦ ለማሪያምና ጣና ቂርቆስ መካከል አንዷ ናት፡፡ በአመሰራረት ቅደም ተከል ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ ሁለተኛዋ ጥንታዊና ብቸኛ ባለታሪክ ደብር ናት፡፡ ገዳሟ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተመሰረተች በመሆኗ 2990 ዓመት ዐድሜ አስቆጥራለች፡፡ የተሰራችዉም በቀዳማዊ ዳዊት የወንድም ልጅ አሚናዳብ አማካኝነት በ982 ዓ.ዓ ነዉ፡፡
የአፄ ገላዉዲዮስ አጽም ያረፈዉ በዚህ ደብር እንቁላል ግንብ በሚባለዉ ነዉ፡፡ በገዳሟ በርካታ ቅርሶች ያሉ ሲሆን ንዋየ ቅድሳት ከ300 በላይ የብራና መጽሃፍት ገድሎች፣ ስዕሎች፣ የነገስታት ዘዉዶች፣ ወንበርና አልባሳት፣ የነገስታት አጽም፣ የጥንት ነገስታት የጦር መሳሪያ ይገኛሉ፡፡ ገዳሙም በድንጋይ ግድግዳ፣ በቆርቆሮ ክዳን የተሰራ ነዉ፡፡
ዓመታዊ ክብረ በዓሏ አጼ ገላዉዲዮስ ታቦተ ልደቷን ከእየሩሳሌም አስመጥተዉ ወደ ቤተ-ክርስቲያኑ ያስገቡበትን ቀን መነሻ በማድረግ ግንቦት 1 ቀን በልደታ እንዲሁም ግንቦት 2 ቀን አጼ ገላዉዲዮስ ከግራኝ ጋር ተዋግቶ ድል አድርጎ የተመለሰበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ይከበራል፡፡

Was this helpful?