ይህ ገዳም ከሐይቅ ከተማ አጠገብ የሚገኝ ጥንታዊ ገዳም ነው፡፡ የተመሠረተው በ9ኛው መክዘ ሲሆን በ13ኛው መክዘ በአቡነ እየሱስ ሞዓ በገዳሙ ውስጥ የወንዶችና የሴቶች ገዳማት ተሸጋገረ፡፡ ለጎብኝዎች ምቹ የሆነ የገዳሙ ሙዚየም ይገኛል፡፡

የሕይቅ እስጢፋኖስ ገዳም በኋላ ዘመን በሸዋ እና በጣና ዙሪያ ገዳማት የመሠረቱ አባቶች የወጡበት ነው፡፡ ታዋቂው ደራሲ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የዳጋው አባ ኂሩተ አምላክ፣አቡነ ጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፣ የመቄቱ አቡነ አሮን፣ የዚህ ገዳም ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ንጉሥ ይኩኖ አምላክም በዚህ ገዳም ተምሯል፡፡

ገዳሙ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲ በመባል የታወቃል፡፡ በውስጡ 800 ተማሪዎች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነበረው፡፡ የገዳሙ መጻሕፍት ከእርስ በርስ ጦርነቶች በመትረፋቸው የአክሱምን ዘመን ከመካከለኛው ዘመን የሚያገናኙ የታሪክ መዛግብት ሆነዋል፡፡   

ገዳሙ በርካታ ቅርሶችን የያዘ ሙዝየም ያለዉ ሲሆን የሚጥመውን የሀይቅ ዓሳ እየተመገቡ በሀይቁ እየተዝናኑ መጎብኘት ይችላሉ፡፡ በተጨምሪም ገዳማዊያኑ በልማት የሚታወቁ ሲሆን የእደጥበብ ውጤቶች፣ የአትክልት ምርትና  እንስሳት ማድልብ ስራ የሚሰሩ በመሆኑ መሸመት ይችላሉ፡፡ ንግስ በዓሉ መስከረም 15ና ህዳር 26 በድምቀት ይከበራል፡፡

ሐይቅ እስጢፋኖስ

Was this helpful?

Stay Nearby

Nearby Accommodations

Find places to stay near this destination.

Travel Essentials

Banking Services Nearby

Find nearby banks and essential visitor services.

Banking Service

CBE

Hayke Estfanos

Mobile & Web Banking: USSD (*889#, *812#, etc.), mobile apps, and internet banking for transfers, utility bill payments, and airtime purchases. Interoperable Mobile Wallets: Direct 2-way wallet-to-bank transfers integrated with Telebirr and M-Pesa. Card & ATM Services: Debit card issuance, cardless cash-outs, local POS payments, and Visa/Mastercard virtual card creation.Micro-Loans & BNPL: Instant collateral-free digital micro-credit (e.g., CBE Beje, Dashen DubeAle, Telebirr Sanduq/Endekise).

2:30-11:30

Traveler Testimonials

Share your experience to help other travelers plan their visit.

1 Testimonial

Add Your Testimonial

Your email address will not be published. Required fields are marked *