ከደሴ በስተ ምዕራብ በኩል 167 ኪ/ሜ ላይ ከምትገኘዉ የከለላ ዋና ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ 46 ከ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ የተመሰረተዉ በ2ቱ አባቶች ነዉ፡፡
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም የደብረ ዳሞን ገዳም የመሰለ አቀማመጥ ያለው ሲሆን አባ ጊዮርጊስ በእጃቸዉ ከአንድ ቋጥኝ የፈለፈሉት ነዉ፡፡ ገዳሙ 8 በሮች፣ 8 ምሰሶዎችና 5 የቅዳሴ ስርዓት የሚፈጸምባቸዉ ክፍሎች ቤተ-ልሄምና ሌሎች ፀሎት ማድረጊያ ፍልፍሎች አሉት፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የአባ በፀሎተ ሚካኤል ፍልፍል ዋሻ በአቀራረጹ አስደናቂ ሲሆን የሚገኘዉ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ካለበት ቋጥኝ ስር ነዉ፡፡ በተጨማሪም አገልግሎት የማይሰጡ የአባ ነብሮና የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፍልፍሎች ይገኛሉ፡፡ አምባው ልክ እንደግሸን ደብረ ከርቤ ባለአንድ በር ብቻ ሲሆነ ራሱን ያስከበረ ውብ ተፈጥሮ አለው፡፡
አባ ጌዮርጊስ ቀዳሽ መነኩሴ ብቻ አልነበረም ይልቁንም የስነ-ጥበብ ሊቅ የህንጻና የድልድይ መሀንዲስ፣ አስተማሪ፣ ጸሀፊና ደራሲ ነበሩ፡፡ ለዚህም በአምባው ላይ ከሚታዩት ህያው ስራዎቻቸው በእጃቸው ከፈለፈሉት ፍልፍል የዋሻ ገዳም በተጨማሪ፡- ከ15 በላይ የውኃ ማቆሪያ ጉድጓድ፣ ከደረሷቸው ከ40 በላይ መጽሀፍት በገዳሙ15ቱ ይገኛሉ፡፡ በአባ ጽጌ ድንግልና በጋሽጫ መካከል ወለቃ ወንዝ ላይ በሁለቱ አባቶች ጸሎት የተሰራው የወለቃ የአለት ድልድይ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ከመጽኀፍቶቹ መካከል መጽሀፈ ሚስጥር፣ መጽሀፈ ሰአታት፣ እንዚራ ስብሀት፣ ህይወተ ማርያም፣ ውዳሴ መስቀል፣ ተአምኖ ቅዱሳን፣ አርጋኖን፣ ፍኖተ ብርሀን፣ ውዳሴ ስብሀት፣ ውዳሴ ሀዋሪያት፣ ክብረ ቅዱሳን፣ ጸሎተ ዘበአት ቤት፣ መኣዛ ቅዳሴ፣ ፍሬ ሐዋሪያት፣ ጸሎተ ፈትቶ፣ ሰላምታ ዘሰሙነ ህማማት ወዘተ… የታተሙና ነጮች እያሳደዱ የሚፈልጓቸውና የመላ ሀገራችን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት የሚጠቀሙባቸው ሀብቶቻችን ናቸው፡፡ ዛሬም የገዳሙ መነኮሳት በግንብ ቤት ስራና በእደጥበብ ስራቸው የላቁ ናቸው፡፡ ክብረ በአሉም በእለተ ጽንሰታቸው ጥቅምት 3 ቀንና የልደትና እረፍታቸው ቀን ሀምሌ 7 ቀን በደማቅ ይከበራል፡፡
Was this helpful?