የአሆላሎ የልጃገረዶች ጨዋታም በውስጡ በርካታ ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን የያዘ በመሆኑ በተለያየ የህዝብ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ክብረ በዓላት ላይ ይከወናል፡፡ ክዋኔው ከፎክሎር ዘውጎች ውስጥ በትውን ጥበባት /performing Art/ የሚካተቱ ሲሆን በውስጡም ሐገረ-ሰባዊ ልማዶች ሆነው የምህበረሰቡ መገለጫ የሆኑ ሌሎች ክዋኔዎች አሉ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ከሚዘወተሩ ባህላዊ ክዋኔዎችና ሀገረ-ሰባዊ ጨዋታዎች ውስጥ በማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች /intangible cultural heritage/ የሚካተተው ²የአሆለሌ² የልጃገረዶች ጨዋታ ነው፡፡

ይህ ጨዋታ በዋነኛነት የሚከወነው በልጃገረዶች ሲሆን፣ ወጣት ወንዶችም በሆታና በጭፈራ እየታገዙ የትዳርና የፍቅር ጓደኝነትን ለመመስረት ይህን የአሆለሌ ጨዋታ አጋጣሚውን ይጠቀሙበታል፡፡

የአሆለሌ ጨዋታ የራሱ የሆነ የመከሰቻ አጋጣሚዎችና የሚከናወንበት ወቅት አለው፡፡ እነሱም የጥምቀት፣ የገና፣ የኢድ፣ የጥር ሚካኤል፣ ጥር 21/አስተሪዮ/ ማሪያም፣ አረፋ፣ ሰርግ ዋናዋናዎቹ ሲሆኑ በተናጠልም ቢሆን በከብት ጥበቃና በእንጨት ሰበራ ወቅትም ሲዜሙ ይስተዋላሉ፡፡

እንደወረዳዎቹና እንደከዋኞቹ ቀበሌዎች የአየር ንብረት፣ ባህላዊና አካባቢያዊ ሁኔታ አለባበሳቸው፣ አጊያጊያጣቸውና የጸጉር ስሪታቸው የተለያየ ቢሆንም በእነዚህ በዓላት ላይ የተሻለ አለባበስና የጸጉር ስሪት ይታያል፡፡ በደቡብ ወሎ በተለይም በምስራቅ

ወረዳዎች ይከወናል፡፡

ከጎፈሬው በላይ ይውላል ሚዶው፣

እኔ እፈራዋለሁ ማን ብየ ልጥራው፡፡

                       የቆላ ደረባ ይመረጋል በበት፣

             ጎፈሬው ይመስላል ንብ የሰፈረበት፡፡ በማለት ያዜማሉ፡፡

በባህሉ በተዋጣለት የፀጉር አበጣጠርና አለባበስ የተዋቡ ጎረምሶች በሽቦ የተጠመጠመውና ከታች ብረት /ጅንፎ/ የገባበት ዱላ/ ሽመል/ እየያዙ ነጠላ ኩታቸውን በማጣጠፍና ትከሻቸው ላይ ጣል አድርገው ሽመላቸውን ወደ ላይ በመያዝ ²ዋርዳው ሽቦ² ²የሚሌው አውሬ² ጎራዴው ሰው በላ ወዘተ …. በማለት የሆታ ዜማዎችን እያዜሙ በድግግሞሽ ²ሆ² ይላሉ፡፡

       ትመታ እንደሆነ በደንብ አርገህ ምታ፣

       አትመታ ከሆነ ልቀቅ የሰው ቦታ፡፡

       የሚሌው አውሬ ፣የሚሌው አውሬ፣

            አልመጣም ዛሬ፡፡

     የተሁሌ ልጆች ጥቃቅኖቹ፣የአምባሰል ልጆች ጥቃቅኖቹ፣

     ይናደፋሉ እንደንቦቹ፡፡…በማለት

ህብረታቸውንና አንድነታቸውን ያጠናክሩበታል፤ ወንድማማችነትን ይመሰርቱበታል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታም ከትጭጭት በኋላ ሚዜ በመሆን ይረዳዳሉ፡፡ ይህም ለሰላምና ለመፈቃቀር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡

በሌላ መልኩ በዚህ የተጀመረው ጓደኝነት ከሀሳብ አልፎ በገንዘብ የመረዳዳት ባህልን ያዳብራል፡፡

        በል ስደድልኝ የጅህን ሎሚ፣

        ሆኛለሁና ልቤን ታማሚ፣

        ይሄ ምን ይላል ጉተናው ዋሾ፣

        ሲሸሽ አየንው ጌሾ ለጌሾ፡፡

        ይሄ ምን ይላል ጉተናው እንቅብ፣

             ሲሸሽ አየነው ቅብቅብ ለቅብቅብ… በማለት ጀግንነትን እንዲላበስ አካባቢውንና ሀገሩን እንዲጠብቅ ፣ወንድነቱን እንዲያጎለብት በስንኝ ቋጠሮ  ያዜሙለታል፡፡ ጎረምሳውም ዙሪያቸውን እየዞረ በጀግና ሞት! ይሄን ሎሚ ውሰጂ በማለት ሎሚ በማቀበል ፍቅሩን ይገልፅላታል፡፡ ሎሚውን ከወሰደች ለእጮኛነት ፈቃደኛ መሆኗን፣ሎሚ ካልወሰደች ለጮኛነት ፈቃደኛ አለመሆኗን ታሳውቃለች፡፡ በመሆኑም በውበትም ሆነ በሚያወጡት ድምፅ/ቅላፄ/ተመራጭ ይሆናሉ፡፡ ትጭጭት የሚፈፅሙት ወጣቶች የሚገናኙበት እውቅና ለጓደኞቻቸው የሚሰጡበት በመሆኑ ማህበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ ነው፡፡

በሌላ መልኩ ሰላምን ከማምጣት አንፃር ሲታይ ጨዋታው የጎረምሶች የትግል ውድድር የሚካሄድበት፣ከትግሉ በኋላ በአካባቢው ባህል በዳኝነት የሚታረቁበት ቂምና ነገር የሚረሳበት በመሆኑ ፍፁም ጓደኝነት ይመሰረትበታል፡፡ ይህም በማህበራዊ ፋይዳው አንፃር ሲታይ በባህሉ እርስ በራሱ የሚተዳደርበት ህግ መኖሩ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል፡፡

Was this helpful?

Traveler Testimonials

Share your experience to help other travelers plan their visit.

Add Your Testimonial

Your email address will not be published. Required fields are marked *