Recommended Duration 3-4

ለሐይቅ ከተማ ስያሜ መነሻ የሆነው ይህ ሐይቅ የሚገኘው ከከተማዋ 2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ በአማካኝ ከባሕር ወለል በላይ 1950 ሜትር ከፍታ ላይ የተፈጠረው የሎጎ ሐይቅ 35 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት እና 23-88 ሜትር አማካኝ ጥልቀት አለው፡፡ ዝቅተኛው የሐይቁ ጥልቀት 88 ሜትር ሲሆን፣ ከባሕር ጠለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ሐይቁ ለጀልባ ጉዞም ሆነ ዙሪያውን በእግር እና በበቅሎ ለመጓዝ ምቹ ነው፡፡

የለጎ ሐይቅ የዳይመንድ ቅርጽ ያለው ሐይቅ ነው፡፡ አካባቢው በእሳተ ገሞራ የተፈጠረ መሆኑን የነገረ ምድር ተመራማሪዎች ይገልጣሉ፡፡ አካባቢው ከወረባቦ ዝቅተኛ ቦታዎች በ500 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይሄም በማዶ ከሚታየው የአፋር ሦስት ማዕዘን ከፍ ብሎ እንደ ባልኮኒ እንዲቀመጥ አድርጎታል፡፡ የሐይቁ ውኃ በዋናነት ከአርዲቦ ሐይቅ ወጥቶ የሚመጣ ነው፡፡ የሐይቁ መጠን እንደ ዝናቡ ሁኔታ ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በሴፕቴምበር 21/1520 አካባቢውን የጎበኘው ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ በሐይቁ ውስጥ ጉማሬ እና ካትፊሽ ማየቱን ገልጦ ነበር፡፡ በሐይቁ ዙሪያ ያለው መሬትም ሎሚ፣ ብርቱካን፣ እና ኮምጣጣ ሎሚ ተተክሎበት ማየቱን ጽፏል፡፡ የአርመን መዛግብት በ10ኛው መክዘ የነበረው የፋርሶች ወረራ በመሸሽ የአርመን ሰዎች ወደ አካቢቢው መምጣታቸውንና በደሴቱ መቀመጣቸውን ይገልጣሉ፡፡ “ሐይቅ” ማለትም በአርመን ቋንቋ “ደሴት” ማለት ነው፡፡   በሐይቅ ዙሪያ በመጓዝ የአሆላሌ ባህላዊ ጨዋታ እና የአበጋር የሽምግልና ሥርዓትን መመልከት ይቻላል፡፡

Was this helpful?

Location on Map

Travel Essentials

Banking Services Nearby

Find nearby banks and essential visitor services.

Traveler Testimonials

Share your experience to help other travelers plan their visit.

Add Your Testimonial

Your email address will not be published. Required fields are marked *