በወግዲ ቦረና ከለላ፣ለገሂዳና ለጋምቦ ወረዳዎች የሚከወን ሌላው ሀገረሰባዊ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ የአጨዋወት ስርዓቱም በኢትዮጵያ አዲስ አመት /እንቁጣጣሽ/ ዕለት ማታ የአዲሱ አመት ማብሰሪያ ችቦ ይቀጣጠልና መስቀል ደመራ ቦታ ‹‹እዮሃ! እዮሃ! እዮሃ!›› እየተባለ ይኬዳል፡፡ የችቦ ማብራት ስነ-ስርአቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መላው ቤተሰብ ወደ ቤት ይገቡና ለበዓሉ የተዘጋጀውን ምግብና መጠጥ ቀርቦ ይመገባሉ፡፡ከዚህ በኋላ የሰፈሩ ጎረምሶች ከደመራው ቦታ ተሰባስበው ችቦ በመያዝ በህብረት እንዲህ እያሉ ይወጣሉ፡፡

Was this helpful?
it nice