ከአዲስ አበባ 361 ኪ/ሜ፣ ከደሴ 38.5 ኪ/ሜ ከኮምቦልቻ ከተማ 15.5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በቃሉ ወረዳ የሚገኝነዉ፡፡ መስጅዱ በአጼ ቴወድሮስ ዘመነ መንግስት በሃጅ ሰይድ ቡሽራ የተመሰረተ ነዉ፡፡
ሃጅ ቡሽራ በሰሜን ሸዋ በኢፋት አውራጃ አንኮበር ተወልደው በሃገር ዉስጥና በሃገር ውጭ በሱዳንና በሳኡሲ አረቢያ ለ25 ዓመታት የእስልምና ትምህርት በስፋት ተምረዉ ወደ ሃገራቸው በመመለስ በርካታ ምሁራንን ያፈሩና ከ500 በላይ ኪታቦችን የፃፉ ምሁር ናቸዉ፡፡
የእኒህ ታላቅ ሰዉ መቃብርም በዚሁ በመስጅዳቸዉ ይገኛል፡፡ መዉሊድ በከፍተኛ ድምቀት በዚህ መሰጅድ ይከበራል፡፡
Was this helpful?