የጀማ ንጉሥ መስጅድ ከሐይቅ ከተማ 67 ኪ.ሜ እንዲሁም ከአልብኮ ወረዳ ዋና ከተማ ሳልመኒ ደቡባዊ አቅጣጫ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው የሚገኝ፡፡ መስጅዱ በ1756 ዓ/ም በታላቁ የእስልምና ምሁር ሐጅ ሰይድ ሙጃሂድ የተቆረቆረ ነው፡፡

ታላቁ ምሁር 1736 ዓ/ም ገደማ እንደተወለዱ፣ በ1756 ጀማ ንጉሥን እንደቆረቆሩ እና በ1798 እንዳረፉ ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

የጀማ ንጉሥ መስጅድ የነብዩ መሐመድ /ሰ.ዐ.ወ/ የልደት በዓል /መውሊድ/ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተከበረበት ቦታ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በየዓመቱም በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በብዙ ሺህ የሚቆጠር የሃይማኖቱ ተከታዮች ጀማ ንጉሥ ይገኛሉ፡፡ በጀማ ንጉሥ የመውሊድ በዓል በተከታታይ ለ3 ቀናት ያህል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው፡፡

Was this helpful?

Traveler Testimonials

Share your experience to help other travelers plan their visit.

Add Your Testimonial

Your email address will not be published. Required fields are marked *